ተግባር እና ኃላፊነት
የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽሕፈት ቤት በአብክመ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 263/2011 አንቀፅ 13(2) የተደራጀ እና በተሻሻለው የክልሉ የአስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 280/2014 አንቀጽ 42 ፊደል ተራ “መ” መሠረት የቢሮው አካል የሆነ ጽ/ቤት ነው፡፡ ጽሕፈት ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 263/2011 ዓ.ም ከተደራጀ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
