የቢሮው ኃላፊ መልዕክት

አቶ ብርሃኑ ጎሽም
የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን የማስከበር፣የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች የማስከበር፣የወንጀል ሕጎችን የማስፈፀም፣የወጡ ህጎችን ተፈጻሚነት የማረጋገጥ፣የሚያወጣቸው ህጎች ላይ እና የሚወስናቸው ትላልቅ ውሣኔዎች ላይ የክልሉን መንግስት የማክበር፣የመንግስትና የሕዝብ መብትና ጥቅም የማስጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቷል፡፡
ይህንን ኃላፊነቱን በአግባቡ የሚወጡ እና በህዝብ ዘንድ ታማኝነትና ተቀባይነት ያለው ተቋም ለመፍጠር የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በማቀድ አዳዲስ ህጎችን በማዘጋጀት፣ነባር ህጎችን በማሻሻል፣አደረጃጀቶችን በማጠናከር፣አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን በማዘጋጀት ሕዝብንና መንግስት የሚጠብቁትን ፈጣን፣ተደራሽ እና ጥራት ያለው የፍትሕ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በሂደቱም ወንጀለኛን የማስቀጣት፣በወንጀል የተወሰደን ሃብት የማስመለስ፣የመንግስትንና የሕዝብን ጥቅም የማስጠበቅ፣ጥራት ያላቸውን ህጎች የማዘጋጀት፤ ተቋሙን ምቹና ሳቢ የማድረግ፣ተቋማዊ ተደራሽነትን የማስፋት፣አመራሩንና ባለሙያውን የማብቃት ስራዎችን ለማከናወን ችሏል፡፡
ይህንን ተግባር ለማከናወን በየደረጃው ያላችሁ የተቋማችን አመራሮች እና ባለሙያዎች የጎላ ድርሻ ስለነበራችሁ ምስጋና ይገባችኋል፡፡ ስለሆነም ተግባራችን በአንድ ወቅት ተሰርቶ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ የጀመርነውን የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራን አጠናከሮ በማስቀጠል በሕዝብ ዘንድ ታማኝነትና ተቀባይነት ያለው ተቋም ለመገንባት በየደረጃው የምትገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ሙሉ አቅማችሁን፤ጊዜያችሁን እና እውቀታችሁን ከላቀ መልካም ሥነ-ምግባር ጋር በማቀናጀት የተጣለባችሁን ኃላፊነት ልትወጡ ይገባል፡፡
ስለ ቢሮው
ዜናዎች | News
የአማራ ክልል ዐቃብያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ የተለያዩ ውሳኔወችን አሳለፈ።
የአማራ ክልል ዐቃብያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ የተለያዩ ውሳኔወችን አሳለፈ።...
Read Moreየፍትሕ ቢሮ የሶስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ።
የፍትሕ ቢሮ የሶስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ። ባህርዳር ፣ሰኔ...
Read Moreዋና ዋና አገልግሎቶች
በሕግ ጉዳዮች ረገድ የክልሉን መንግስት ዋና አማካሪ ሆኖ መስራት
የውል ሰነድ ዝግጅትና ውል ምርመራ ለመንግስት ቢሮዎችና ለልማት ድርጅቶች
ወንጀል ፈፅመው ሲገኙ ደግሞ ህጉ በሚፈቅደው ልክ ተከራክሮ ማስቀጣት፣ታርመውና ታንፀው እንዲወጡ መከታተል
የፍትሐብሔር ጉዳዮችን በተመለከተ የክልሉ ህዝብና መንግስት መብቶችና ጥቅሞች ህጋዊ ወኪል በመሆን ይስራል
የንቃተ ህግ ትምህርት መስጠት ለማህበረሰቡ ቅድመ ወንጀል ለመከላከል



