በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት
ተግባር እና ኃላፊነት
በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ፍትህ ቢሮው የስራ ክፍሎችን በ2015 ዓ.ም መጀመሪያ እንደገና አደረጃጃት ሲሰራ በአዲስ ከፍቶ ወደ ስራ ያስገባው የስራ ክፍል ነው፡፡ የስራ ክፍሉም በዋናነት በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስመለስ በሚቻልባቸው በሙስና ወንጀል ህጎች (አዋጅ ቁጥር 434/97 በአዋጅ ቁጥር 882/2007 እንደተሻሻለው እና ሌሎችም)፣ በወንጀል የተገኘ ሀብት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኛን በገንዘብ መርዳት ህግ (አዋጅ ቁጥር 780/2005)፣ በሰው የመነገድ እና በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር የማሻገር ህግ (አዋጅ ቁጥር 1178/2012)፣ የወንጀል ህግ እና በመሳሰሉ የንብረት ውርስ በሚያስከትሉ የሀገሪቱ ህጎች በጠቅላላው ለዐቃቤ ህግ የተሰጠውን ስልጣን እንዲሁም ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት በማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡
