የግዥ፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት
- አመታዊ የመስሪያ ቤቱን የጸደቀ በጀት ይመዘግባል፣ በየጊዜው የጸደቀው የመስሪያ ቤቱ በጀት በመስሪያ ቤቱ የባንክ አካውንት ገቢ እንዲደረግ መጠየቅ፣ ከመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የመደበኛ እና የካፒታል ገቢ መሰብሰብ፣ እጥረት ላለባቸው የሂሳብ መደቦች የበጀት ዝውውር መፈጸም፣ ተጨማሪ በጀት መጠየቅና መቀበል፤
- በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት የማይሰጡ አላቂና ቋሚ ዕቃዎች እንዲለዩ በያደርጋል በህግ መሰረት ወቅታዊ እርምጃ መውሰድ፣
- የቋሚ ንብረት መዝገብ በአግባቡ መያዙን፤ ንብረቶች መለያ ቁጥር አግኝተው መመዝገባቸውን፣ ቋሚና አላቂ ንብረቶች በንብረት አስተዳደር መመሪያዎች መሠረት ገቢና ወጪ መደረጋቸውን እና ለተፈለገው ዓላማ መዋላቸውን ማረጋገጥ፣
- የግዥና ንብረት አስተዳደር ውሳኔዎች ህግን መሰረት አድርገው የተወሰኑ መሆናቸውን ማረጋገጥ፤
- በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ ምላሽ ይሰጣል፤ ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል ፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
በመስሪያ ቤቱ ተፈጻሚ የሚሆኑና ዳይሬክቶሬቱን የሚመለከቱ ዝርዝር የአሰራር መመሪያዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፤
