የሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሀላፊነት

  • የመንግሥት ሠራተኞችን በሚመለከት የሚወጡ መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት በማድረግ ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው  ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ በማድረግ ስራዎችን ያከናውናል፣
  • አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት ሠራተኞችን መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
  • በቢሮው ላሉ ሰራተኞች የሚፈልጉትን ማስረጃ በሚጠይቁት አግባብ ትክክለኛነቱን ከማህደራቸው በማረጋገጥ ይሰጣል፤
  • በቢሮው ስር ያሉ የዞን ፣የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ፍትህ መምሪያዎች እና ፍትህ ጽ/ቤቶች የስራ መደብ ጥያቄወችን እና የደረጃ ይሰተካከልልን ጥያቄወችን በመቀበል ከአብክመ ሲቪል ሰረቪስ ኮሚሽን ያስፈቅዳል፤
  • በቢሮው የሚቀርቡ የዲስብሊን ክስ በማጣራት ለበላይ ኃላፊው የውሳኔ ሃሳብ አስተያየት ያቀርባል የሚሰጠውን ውሳኔም እንዲፈጸም ያደርጋል፤
  • የስራ ልብስና የስራ መሳሪያ የሚያስፈልጋቸው ልጆች በወቅቱ እንዲያገኙ ለግዥና ፋይናንስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያሳውቃል፡፡
  • በራሳቸው ፈቃድም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች የሚለቁ ሰራተኞችን መልቀቂያ ክሊራንስ ይሰጣል፤
  • በመመሪያው መሰረት የወሊድ ሰርትፊኬት ላቀረቡ ሰራተኞች የወሊድ ፈቃድ ይሰጣል፤
Scroll to Top