የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትተግባር እና ኃላፊነቶች የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ ሆኖ በስሩ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክትረ እና ዐቃቢያነ ሕግ እንዲሁም አስተዳደር ሰራተኞችን የያዘ ነው፡፡ ዳይሬክቶሬቱ በወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ ስር ካሉት ዳይሬክቶሬቶች ጋር በወል የተሰጡ ተግባር እና ኃላፊነቶች አሉበት፡፡ ይኸውም፤ የወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ፡- በፌድራልም ሆነ በክልል ፖሊስ በተጣራ የምርመራ መዝገብ ላይ መርምሮ መወሰን፣ ተከራክሮ ማስወሰን፤ በፖሊስ የተጀመረ የኢኮኖሚ ወንጀል ምርመራ የምርመራ አካሄዱን ሕጋዊነት ይከታተላል፣ ይመራል፣ በተጀመረ የወንጀል ምርመራ ላይ ሪፖርት እንዲቀርብና ምርመራው በአግባቡ ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል፤ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ