
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የ2016 በጀት አመት የፍትሕ ዘርፍ የሪፎርም እቅድ አፈጻጸም በመገምገም የ2017 በጀት አመት አቅድ ለፍትህ መምሪያ ኃላፊዎችና ለማኔጅመነቱ አባላት በ29/11/2016 ኦሬቴሽን ሰጠ፡፡
በ2016 በጀት አመት አቅድ ውስጥ በአስራ አንዱ ግቦች ውስጥ የተከወኑ ተግባራትን የሚያመላክት ሰነድ በቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም የቀረበ ሲሆን ከየዞኑ የመጡ የመምሪያ ኃለፊዎች በችግርም ውስጥ ሁነው የሰሯቸውን ስራዎች አቅረበዋል፡፡
ለዚህም የፍትህ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስልጠና ከተሰጠ በኃላ እቅድ አቅደው ወደታች ማውረደ ፤ የሚመለከታቸውን አካላት በመለየት የቴክኒክ ኮሚቴ አዋቅረው ወደስራ እንደገቡ ገልጸዋል፡፡አያይዘውም በጀት በመመደብ ቢሮአቸውን በተገቢው በማደራጀት ሳቢና ማራኪ ማድረግ፣ከስቪክ ማህበራት ጋር ከሰነድ አሰጣጥና ከምስክርነት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ውይይት ያካሄዱ ስለመሆኑ፣ የአፈጻጸም ውስንነት በታየባቸው ተግባራት ላይ የዳሰሳ ጥናቶች ማካሄድ እንደቻሉ፣ የተሰሩ ስራዎችን በሚዲያ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራ መሰራቱ ፣የአመራርና ሙያተኛ የማጥራት ስራ መጀመሩ ፣የቴክኖሎጅ አጣቃቀም መልካም የሚባል ጅምር መኖሩ በጥንካሬ የታዩ ስራዎች ቢሆንም የምስክር ኣቀራረብ ችግር በመኖሩ የሚዘጉ መዛግብት መኖራቸውና በሚጠበቀው ልክ የአገላግሎት አሰጣጥ ላይ አለመደረሱ የተገመገሙ ነጠቦች ሁነዋል፡፡
በግምገማው የሚታዩ ውስንነቶችን ለመሻገር በቁርጠኝነት ሪፎርሙን እውን ማድረግ እንደሚገባ ያሳሰቡት የቢሮው ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም የ2017 በጀት አመት እቅድ በተቀመጡ ግቦች ዝርዝር ማስፈጸሚያ ተግባራት አመላክተው ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ከነመፍጽሔቸው አቅረበው የቀጣይ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩን አጣቀለዋል፡፡
