በግድያ ወንጀል የተከሰሱ ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ።
=======================
ተከሳሸች ፦ 1ኛ/ እንድሪስ ሁሴን ካሚል፣
2ኛ/ መሀመድ እንድሪስ ሁሴን፣
በቀን 17/03/2016 ዓ/ም በደዋጨፋ ወረዳ ምክንያቱ ባልታወቀ መነሻ ሟች መሀመድ እንድሪስ አደም የተባለውን ግለሰብ አባሪ ተባባሪ በመሆን በጩቤ በመውጋት እና በድንጋይ በመደብደብ ከባድ ጉዳት አድርሰው ገድለዋል የሚል መረጃ ለፖሊስ የደረሰው በመሆኑ የወረዳው ፖሊስ ምርመራ አጣርቶ እና አደራጅቶ ለኦሮሞ ብሄ/አስ /ዞን ፍትህ መምሪያ ልኳል።
መዝገቡ የደረሰው የመምሪያው የልዩ ልዩ ወንጀል የስራ ሂደትም በወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 539/1/ሀ መሰረት ክስ መስርቶ በማቅረብ በኦሮሞ ብሄ/አስ /ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱ የከሳሽን እና የተከሳሽን ክርክር አዳምጦ እና መዝገቡን መርምሮ ሰኔ 19/2018 ዓ /ም በዋለው ችሎት ተከሳሾችን ጥፋተኛ በማለት 1ኛ ተከሳሽን በ14 ዓመት፣ 2ኛ ተከሳሽን በ15 ዓመት፣ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል።
ምንጭ :- የኦሮሞ ብሄ/አስ /ዞን ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀል የስራ ሂደት


