በጠለፋ ወይም በእገታ ወንጀል ዙሪያ የሕግ ማብራሪያ ተሰጠ።

በጠለፋ ወይም በእገታ ወንጀል ዙሪያ የሕግ ማብራሪያ ተሰጠ።

ባህር ዳር ሰኔ 11/2018 ዓ/ም (ፍትህ ቢሮ)

አያሌው አባተ ዶ/ር የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ጠቅላይ ዐ/ሕግ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ጠለፋ ወይም እገታ ወንጀሎች የጸጥታን እና የሰላም መታወክን ታክኮ በተለያዩ አካላት በግለሰቦች መብት እና ነፃነት ላይ የተደቀነ እጅግ አሰቃቂ እና አደገኛ ወንጀል መሆኑን በመግለፅ አብራርተዋል።

ጠለፋ(kidnapping) በአሁኑ ወቅት በተለያየ መንገድ እና ለተለያየ ዓላማ ወቅታዊ የፀጥታ ችግሮችን ታክኮ በሰፊው እየተፈጸመ ቢሆንም በክልሉ ከሕዝባችን እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን መከላከል፣ መቆጣጠር እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እየተቻለ መሆኑን ገልጸዋል። ስለሆነም ወንጀሎችን ለመከላከል እና ምለሽ ለመስጠት በወንጀል ፍትህ አስተዳደሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን ገለጹ ።

ግለሰቦቾ በላባቸው ያፈሩት ንብረት እንዳይነጠቅ ወንጀለኛም ከሰራው ወንጀል ምንም አይነት ጥቅም እንዳያገኝ ከፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፣ እስከ ታችኛው መዋቅር እና ከፌደራል ፣ ከአጎራባች ሌሎች አስፈጻሚ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር ስራዎች እየተሰሩም ነው ብለዋል።

አክለውም ጠለፋ ብቻ ሳይሆን የውምብድና ወንጀል አሁን አሁን ሀብት የአለው ንብረት አለው የተባለ ህብረተሰብ ላይ ስራዬ ተብሎ እና ታርጌት እየተደረገ የሚፈጸም ወንጀል እየሆነ እንደመጣም አብራርተዋል።

ይኼ በመሆኑም ቢሮው ወንጀሉን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አደረጃጀት ፈጥሮ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ በጉዳዩ ላይ እየተሰራበት ነው ብለዋል።

እገታ ወይም ጠለፋ ወንጀል በደንብ በተደራጀ መልኩ የሚፈፀም በመሆኑ ለውጤታማ አፈጻጸም ካለሕዝቡ ተሳትፎ አስቸጋሪ ባህሪ ያለው እንደሆነም አብራርተዋል።

በመጨረሻም ጠለፋ/እገታ እና ውምብድና በሰው ልጅ ሕይወት ደህንነት በንብረት ላይ የሚፈጸም ኢሰብአዊ ወንጀል በመሆኑ ካለ ማህበረሰቡ ተሳትፎ የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩ ውጤታማ ሊሆን ስለማይችል ማህበረሰቡ ራሱ ክትትል አርጎ ምስክር ሆኖ ከጸጥታ ተቋማት ጋር በመሆን በይፋ ሊያወግዘው እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተው አሳስበዋል።

ጠለፋ/እገታ/ በክልሉ ለተለያዩ ዓላማዎች (ለጋብቻ ጠለፋ፣ ለድርድር የሚደረግ ጠለፋ፣ ለዝናና የበላይነትን ለማሳየት የሚደረግ) የሚፈጸም ሲሆን በዋናናት በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ የሆነው መጤ እና ከባሕላችን፣ ከእሴቶቻችን ያፈነገጠው ጠለፋ ሰውን ጠልፎ ሰውሮ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠየቅበት ለቁስ/ለገንዘብ ሰው የሚገደልበት/የሚበዘበዝበት/የሚራቆትበት ወንጀል አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል።

ወንጀሉ እንዳይፈጸም የመከላከልና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ይሰራል ተፈጽሞ ሲገኝ ቢሮው ከፖሊስ ጋር ሆኖ መርምሮ ውጤታማ ጥራት ያለው ክስ በመመስረት ለፍ/ቤት አቅርቦ ወንጀለኛው ተይዞ በሚመጣበት ጊዜ ቅድሚያ ተሰጥቶ ቅጣት የማስቀጣት ስራ ይሰራል ነው ያሉት። በጠለፋ ወንጀሎች ዙሪያ በርካታ (ከ400 በላይ) የወንጀል ክስ መዝገቦች ቀርበው እስከእድሜልክ ጽኑ እሰራት አስተማሪ ቅጣት በየዞኖች መሰጠቱን ገልጸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top