ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት 12 ወራት የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ዕቅድ አፈጻጸምን ከዘርፋ ዳይሬክተሮች ጋር ገመገሙ።
የ2018 በጀት ዓመት 12 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ሪፖርትን የገመገሙት የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ም/ኃላፊ እና የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ አያሌው አባተ (ዶክተር) ናቸው፡፡
በበጀት ዓመቱም በተደረገው ግምገማ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውጤታማነትን በማሳደግ የወንጀል ምርመራ መዛግብት የመወሰን ቅልጥፍናን98% ለማድረስ ታቅዶ99.41% ማድረስ ተችሏል፡፡ በመዛግብት ሲታይ 22,861 መዛግብት ቀርበው 21,731 መዛግብት ውሳኔ እንዲያገኙም ተደርገዋል፡፡
የክስ አይቀርብም የውሳኔ ጥራት ምጣኔን 98.5% ለማድረስ ታቅዶ 603 መዛግብት ውስጥ 580 ውሳኔ የተሰጣቸው መዛግብትን በመመርመር 559 መዛግብት ሲጸድቁ 21 መዛግብት በመሻራቸዉ አፈፃፀሙ 96.37% እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ በቀጥታ ክስ የወንጀል መዛግብት የዐቃቤ ህግ ተከራክሮ የማስቀጣትአቅምን 90% ለማድረስ ታቅዶ 90.82% መፈጸም እንደተቻለ ነው መረዳት የተቻለው፡፡ በመዛግብትም ከቀረቡት 19,403 ለፍርድ ቤት ከቀረቡት ውስጥ 9,609 መዛግብት ላይ ውሳኔ እንዲያገኙ መደረጉን እና 8,727 መዛግብት በማሸነፍ 882ቱ መዛግብት በፍ/ቤት ነፃ ናቸው እንደተባለ ነው በሪፖርቱ የቀረበው፡፡
በዚሁ ዘርፍ ስር ከሚገኙት አንዱ በሴቶች፣ በህጻናት፣ በወጣቶች፣ በአረጋውያንና በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በቀጥታ ክስ ከቀረቡት 479 መዛግብት ውሰጥ 294 መዛግብት ውሣኔ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል፡፡ ውሳኔ ከአገኙት ውስጥም 244 መዛግብት ማሸነፍ የተቻለ ሲሆን 50 መዛግብት በፍ/ቤት ነፃ በመባላቸው የተዘጉ ናቸው ተብሏል፡፡ ሌላው ትኩረት በመስጠት የሚሰራበት በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል የመከላከልና አጥፊዎችን በህግ የመጠየቅ ውጤታማነትን 82.5% ለማድረስ በእቅድ ተይዞ 84.52%/ መፈጸም የተቻለ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
በወንጀል ጉዳይ የተመዘበረ ሃብትን ከማስመለስአንጻር ብር 470,775,233.70፣ መሬት 3,249,750ካ/ሜቦታ፤ ከዋስትና 12,620,451.00 ብር እንዲሁም በኤግዚቢት ከተቀመጡት ከጦር መሳሪያ፣ ከአፈር ማዳበሪያ፣ ከቤንዚንና ናፍጣ፣ ከኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ ከቤት ዕቃዎች እና ከሸቀጣሸቀጥ እህል፣ ከቅባት እህል እና ከቅመማቅመም፣ ከእንስሳት፣ ከሰውና እንስሳት መድሃኒት 789,444,194.39 ብር የሚገመት ንብረት ለመንግስት ገቢ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ ከወንጀል ጉዳይ ከቅጣት 19,213,467.00 ብር ለመንግስት ገቢ ማድረግም ተችሏል ፡፡
የወንጀል የገንዘብ ቅጣት ከሚጠበቀው 21,247,300.00 ብር የሚፈለግ ሲሆን 19,213,467.00 ብር ገቢ ማድረግ መቻሉን እና አፈፃፀሙ 90.43% እንደሆነ ነው መገንዘብ የተቻለው፡፡ በወንጀል የተመዘበረን የመንግስትና የህዝብ ሃብት ለማስመለስ የሚያስችል ሀብት 3,789,716,572.38 ብር ከያዙት 92 ምርመራ መዛግብትም 3ቢሊዬን542ሚሊዬን121ሺ3መቶ23 ብር ከሰላሳ ሳንቲም ውሳኔ ማገኘት የተቻለ መሆኑን ከማብራሪያው ለመረዳት ነው የተቻለው፡፡ ቀሪ 247ሚሊዬን595ሺ.2መቶ49ብር የያዙ 5 መዛግብትበ ምርመራ ላይ መሆናቸውም በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በቀረቡ የዋስትና ጥያቄዎች በወቅቱ እና በአግባቡ ያለው የዋስትና አስተያየት መስጠት ውጤታማነትን 97% ለማድረስ ታቅዶ፤ 16,503 መዛግብት ቀርበው 16,348 መዛግብት ላይ ዐ/ህግ በሰጠው መሰረት የተወሰነ ሲሆን አፈፃፀሙ 99.04% እንደሆነ ፤ የዓቃቤ ህግ ይግባኝና ሰበር አቤቱታ መዝገቦች የክርክር ውጤታማነትን 72% ለማድረስ ታቅዶ፤ 1,773 መዛግብት ለፍ/ቤት ቀርበው በፍርድ ቤት ከተወሰኑት 1,028 መዛግብት ዉስጥ 735 መዛግብት ማሸነፍ የተቻለ ሲሆን 293 በመሸነፍ ውሳኔ ያገኘ ሲሆን አፈፃፀሙ 71.50% ፤ የፍርደኛ ይግባኝና ሰበር አቤቱታ መዝገቦች የክርክር ውጤታማነትን 90% ለማድረስ ታቅዶ፤ 1,779 መዛግብት ቀርበው በፍርድ ቤት ከተወሰኑት 1,339 መዛግብት ዉስጥ 1,233 መዛግብት ላይ በማሸነፍ አፈፃጸሙ 92.08% ነው፡፡ 106 መዛግብት በመሸነፍ በመሸነፍ ውሳኔ መሰጠቱን ነው በሪፖርቱ የቀረበው፡፡
ምርመራ የሚደረግባቸውን መዛግብት ላይ ወንጀል የፍሬ እና የማካካሻ ንብረት በማሳገድ 45 መዛግብት በ42ቱ ንብረቶች ግምታቸው ብር 112,825,654.29 እና ግምት ያልወጣላቸው 12 ተሽከርካሪዎች፣ እንዲሁም 148,424.35 ካ/ሜትር ቦታ ያለው 19 ቤቶችና ቦታን ጨምሮ በባንክ አካውንት የሚገኝ ገንዘብ 112,825,654.29 ብር ቀርበው በፍ/ቤት እንዲታገድ ውሳኔ ውሳኔ ማሰጠት የተቻለ እንደሆነም ተገልጿ፡፡
የሀብት ማስመለስ ምርመራ የሚደረግባቸውን መዛግብት ላይ የወንጀል ፍሬ እና የማካካሻ ንብረት ማሳገድን 90% ለማሳደግ ታቅዶ፤የዞረውን ጨምሮ 45 መዝገቦች 42 ንብረቶች ግምታቸው ብር 112,825,654.29 እና ግምት ያልወጣላቸው 12 ተሽከርካሪዎች፣ 148,424.35 ካ/ሜትር ቦታ ያለው 19 ቤቶችና ቦታ እንዲሁም በባንክ አካውንት የሚገኝ ገንዘብ ብር 112,825,654.29 ቀርበው በፍ/ቤት እንዲታገድ ውሳኔ ያገኘ ሲሆን አፈፃፀም 100% ማድረግ ተችሏል፡፡
የሀብት ማስመለስ ክስ የተመሰረተባቸውን መዛግብት የመርታት ምጣኔን 91% ለማድረስ ታቅዶ 78 መዛግብት 87,323,244.80 ብር የያዙ ቀርበው 7 መዛግብት 57,268,135.80 ውሳኔ ያገኙ ሲሆን ቀሪዎች በቀጠሮ ላይ ይገኛል፡፡ አፈፃፀም 100% ነው፡።
ልዩ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው የወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ በሽብር ወንጀል ፤በመሰረተ ልማት ስርቆት፣በሰዎች መነገድና ድንበር ማሻገር፤በሴቶች ህጻናትና ወጣቶች፤መሰረተ ልማት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፤በእገታና ጠለፋ፤በሙስና እና ህገ-ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ጉዳዮች ክትትል ማድረግና አጥፊዎችን በሕግ የመጠየቅና የማስቀጣት ስራም እንደተሰራ ነው በሪፖርቱ ማየት የተቻለው፡፡
በመጨረሻም የተቋሙን የአፈጻጸም አቅም የበለጠ ለማጠናከር፣ የሕዝብ አመኔታን ለማሳደግ እና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዙ የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

