የሰሜን ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ እና በስሩ የሚገኙ ወረዳዎች የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ትውውቅ መድክ አካሄዱ።
ባህርዳር መስከረም 07/2019 ዓ/ም (ፍትሕ ቢሮ) የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ትውውቅ የሰሜን ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ የማኔጅመንት አባላት ፤ የዞን ዐቃብያነ ህግ፣አጠቃላይ አስተዳደር ሰራተኞች እና የወረዳ ፍትህ ጽ/ቤቶች ማኔጅመንት አባላትና የወረዳ ዐቃብያነ ህግ፤ የባህር ዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ኃላፊ እና የሰሜን ጎጃም ዞን ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ም/ኃላፊ በተገኙበት የግምገማ መድረክ ተካሂዷል።
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት አቶ ሰጥአርጌ መሰሉ የሰሜን ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ መድረኩ ላይ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ የመንግስት የበላይነት እንዲከበር፣ የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲገነባ፣ ውስብስብ የወንጀል ጉዳዮችን ከፖሊስ ጋር በመሆን በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።
በወንጀል ፍትሕ አሥተዳደር በኩል ወንጀልን ለመከላከል እና የተመዘበረ ንብረትን ለማስመለስ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን አና በአጠቃላይ ከሙስና ወንጀል፣ ከኢግዚቪት፣ከዋስትና፣ ከወንጀል ቅጣት ብር 466,621,388.7 ለመንግስት ገቢ መደረጉ በሪፖርቱ ተመላክቷል ።
በፍትሐብሄር ጉዳዮች የቀጥታ ክስና መልስ አቀራረብ፤ በከሳሽነት ከክስ በፊት በድርድር የመፍታት በከሳሽነት ከክስ በፊት በ152 መዝገብ ብር 26,867,,640.00 እና ከክስ በኋላ በ29 መዛግብት 392,777,487ብር በድርድር መፍታት መቻሉ፤ ክስ በቀረበባቸው ጉዳዮች ንብረት ማሳገድ፤ የቅድመ መከላከል ስራን የውል ረቂቅ የማዘጋጀትና የውል ረቂቅ የመመርመር ፤ነጻ የህግ ድጋፍ በውጤታማነት መሰራቱን በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በሰነዶችና ጠበቆች አገልግሎት ዘርፍ የተመዘገቡ ሰነዶች ብዛት 57,417 ሰነዶችን በማረጋገጥ 182,410,590.42 ብር ገቢ መሠብሠቡ ተገልጿል።
ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በአቶ መንበሩ ማናየ እና በአቶ ሰጥአርጌ መሰሉ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል።
አቶ ሰጥአርጌ መሰሉ ሲያጠቃልሉ በቀጣይ ትኩሰት ሰጥተን የምናሻሽላቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፤ የማህበረሰብ እርካታ እና ህግን ማስከበር፤ ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
የአብክመ ፍትህ ቢሮ የፍትሐብሄር ፍትህ አስተዳደር ዳይሪክቶሬ ዳይሪክቶሬት አቶ መንበሩ ማናዬ የ2018 በጀት ዓመት በወንጀል፣ በፍትሐብሄር ፣በሠነዶቸ እና በሌሎች የስራከፍሎች መልካም የአፈጻጸም ቱሩፍቶች የተመዘገቡበት ወቅት እንደነበረ አውስተው በ2019 በጀት ዓመት የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የዜጎችን የመኖር ዋስትና ማረጋገጥ፣ የህዝብን እና የመንግስት መብት እና ጥቅም ማስከበር ይኖርብናል ብለዋል።
የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ለማሣካት የመምሪያው እና የተዋረድ መዋቅሩ ሰራተኞች ለተግባራዊነቱ ርብርብ ማድረግ ይገባል በሚል መድረኩን አጠቃለዋል።






