የመንግሥት እና የሕዝብ ጥቅምን የሚያስጠብቁ የቅድመ መከላከል ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

የመንግሥት እና የሕዝብ ጥቅምን የሚያስጠብቁ የቅድመ መከላከል ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

ባህርዳር ፣ነሐሴ 27/2018 ዓ/ም (ፍትሕ ቢሮ) የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ የቢሮው አመራሮች፤ ዳይሬክተሮች፣ የቋሚ ምድብ አስተባባሪዎች፣ የዞን ፍትህ ምሪያ ኃላፊዎችች እና የራጅዮፓሊታንት ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት የግምገማ መድረክ አካሂዷል።

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ብርሃኑ ጎሽም በግምገማ መድረኩ ላይ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ የመንግሥት እና የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር በተከናወኑ የሕግ፣ ፍትሐብሔር እና የወንጀል ፍትሕ አሥተዳደር ሥራዎች ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል።

በሕግ እና ፍታብሔር ዘርፍ ክልላዊ የፍትሐብሔር ስትራቴጂ በማዘጋጀት የአሠራር ሥርዓቶችን ማሻሻል ተችሏል። በዚህም በፍርድ ቤት ተከራክሮ የማሸነፍ ምጣኔን በማሳደግ፣ ውሳኔ ከተሰጠበት 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ውስጥ 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብሩን ተከራክሮ ማሸነፍ ተችሏል ነው ያሉት።

በፍርድ ማስፈጸም ሂደት ከተወሰነው 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ውስጥ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብሩ ለመንግሥት ገቢ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።

በሰነዶች፣ በጠበቆች እና በሲቪክ ማኅበራት አገልግሎት ዘርፍ ከ669 ሺህ 600 በላይ ተገልጋዮችን በማስተናገድ እና ከ394 ሺህ 600 በላይ ሰነዶችን በማረጋገጥ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መሠብሠቡ ተገልጿል።

የሕግ አወጣጥን ፍትሐዊ እና ተገማች ለማድረግ በተደረገው ጥረትም በበጀት ዓመቱ 15 አዋጆች፣ 65 ደንቦች እና 31 መመሪያዎች በጠቅላላው 111 ሕጎች በጥራት እና በፍጥነት መዘጋጀታቸውን አንስተዋል። 142 ነባር መመሪያዎች ደግሞ በቢሮው ድረገጽ ተጭነዋል ነው ያሉት።

በወንጀል ፍትሕ አሥተዳደር በኩል ወንጀልን ለመከላከል እና የተመዘበረ ንብረትን ለማስመለስ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን የጠቀሱት ኃላፊው ከፖሊስ የቀረቡ ከ22 ሺህ 800 በላይ የምርመራ መዛግብት ውስጥ ከ21 ሺህ 700 በላይ መዛግብት ላይ ውሳኔ ተሰጥቷል ብለዋል። ውሳኔ ካገኙ 9 ሺህ 609 መዛግብት መካከልም ቢሮው በ8 ሺህ 727ቱ በማሸነፍ የላቀ ውጤት አስመዝግቧል።

አሰራሮችን ለማዘመንና ዲጅታላይዝ ለማድረግ በክልልና በዞን የ ICT ባለሙያዎች የስራ መደብ በማስፈቀድ ቅጥር መፈጸሙንም ገልጸዋል።

በ2019 በጀት ዓመትም ከፖሊስ ጋር የምንመላለሳቸውን ውዝፍ መዛግብት በማጣራት የመንግሥት እና የሕዝብ ጥቅም እንዲከበር አገልግሎት አሰጣጣችን ከመከራከር መከላከል የሚለውን መርህ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አስታውቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top