በከባድ_የሰው ግድያ ወንጀል የተከሰሰው ተከሣሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ ።
=============================
እንጅባራ| ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ/ም(አዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ)
ተከሣሽ….. አስማረ_መላኩ የተባለው ግለሰብ አስቀድመው ለመግዳል በማሰብ ሜያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 5:00 ሰዓት ሲሆን አየሁ ጓጉሣ ወረዳ ቻጃ ክብርታ ቀበሌ ልዩ ስሙ አቫጅ ጋሉ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ሟች ዋሲሁን ታሪክ ይባል የነበረውን ግለሰብ የሟች ቤተሰብ ከዚህ በፊት የተከሣሽን ወንድም ገድሏል በሚል ቂም ተነሳስተው ሟች ከብቶችን ውሃ ለመጠጣት እየሄደ እያለ ተከሣሽ በያዘው ክላሽ ጦር መሣሪያ አከታትሎ በመተኮስ ጀርባውንና ሽንጡን በመምታት ጨካኝ፣ነውረኛና አደገኛ በሆነ ሁኔታ የገደለው በመሆኑ የምርመራ መዝገቡ ለአዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ መደበኛ ወንጀል ተልዕኮ መዝገቡን በጥልቀት በመመርመር የወ/ህ/ቁ 32/1/ሀ እና 539/1/ሀ በመጥቀስ በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ክስ አቅርቦበት ተገቢውን የህግ ክርክር በማድረግ ከጥርጣሬ በፀዳ መልኩ ያስረዱ በመሆኑ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ አሰምቶ ባቀረበችው የመከላከያ ማስረጃዎች ወንጀሉን አለመፈፀሙን ማስተባበል ያልቻለ ስለሆነ የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት በቀን 26/10/2018 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሣሹን በሙሉ ድምፅ ጥፋተኛ ነው ብሏል። ስለሆነ ተከሳሽንም ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ያስተምራል በማለት በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል ።


