የፍትሕ ቢሮ የሶስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ።
ባህርዳር ፣ሰኔ 11/2018 ዓም (ፍትሕ ቢሮ) የፍትሕ ቢሮ ከ2016 እስከ 2018 በጀት ዓመት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም ከማኔጅመንት አባላት ጋር የቢሮው ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም ገመገሙ።
በግምገማ መድረኩ ትራንሰፎርሜሽኑን እውን ለማድረግ የተቀረጹ ግቦችንና ዝርዝር ተግባራት አፈጻጸም የቀረበ ሲሆን የትራንስፎርሜሽን ትግበራውን በተሻለ ለመፈጸም ደንቦች፣ ማንዋሎች ፣ ስትራቴጂዎች እና ሌሎችም በተሻለ መልኩ መፈጸም መቻሉን የማኔጅመንት አባላት ገልጸዋል።
የተሰሩ ስራዎች ሰፊ ናቸው ያሉት የቢሮው ም/ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንዳቸው ሰራው በህጉ መልኩ ከተመለከትነው በርካታ ስራዎች ተጠናቀዋል። በሌላ መልኩ ስራዎች ወደ ትግበራ ሲገባ ቅንጅትን የሚጠይቁ እና ታች ወርዶ መስራትን የሚጠይቅ መሆኑን ተገንዝበን መስራት አለብን ብለዋል።
አቶ ወንዳቸው ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም አኳያ ለተቋሙ ያለውን አስፈላጊነት ተረድተን ልዩ ትኩረት ሰጠን መስራት ፤ የወጡና የጸደቁ ህጎች በዊቬሳይት መጫን፤ ተከሳሾች በሌሉበት የሚወሰኑ ውሳኔዎችን የማሰፈጸም አቅም ማሳደግ፣ የተከሳሽና ምስክር አቀራረብ ፣ ተቋሙን ለሙያተኛውና ለተገልጋዩ ሙቹ ማድረግ፣ የተገልጋይ እርካታ ማረጋጥ እና ሌሎችም ላይ ልዩ እይታ ይዘን እንስራ ሲሉ በትኩረት ተናግረዋል፣
ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ አደረጃጀት በመፍጠር ወደ ስራ ገብተናል ያሉት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ጎሽም ትራንሰፎርሜሽን ትኩረቱ የህግና የአሰራር ስርዓት ላይ ያተከረ እና ተቋም መፍጠር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እኛም በዚህ መልኩ እየሰራን መጠናል ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ብርሃኑ ግሽም እንደገለጹት ስራው ጊዜ፣ እውቀት፣ማንበብና መጻፍ የሚጠይቅ ስለሆነ በኮሜቴ ውስጥ የተሳተፉና የሰሩ አባላት የሚመሰገኑ ናቸው። ስራችን የተቋሙን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም አጎልብቷል ብለዋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም ባለፉት ሶስት ዓመታት በፍትሕ አሰጣጥ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊነት እና በሰው ኃይል አቅም ግንባታ ላይ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በመጨረሻም ኃላፊው ቢሮው የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ለሕዝብ የሚሰጠውን የፍትሕ አገልግሎት ጥራት ለመጨመር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በዚሁ ወቅት ተገልጸዋል።

