የአማራ ክልል ዐቃብያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ የተለያዩ ውሳኔወችን አሳለፈ።
(ሐምሌ 02/2018 ዓ/ም፣ባህር ዳር ፣ፍትህ ቢሮ) የአማራ ክልል ዐቃብያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔወችን ወስኗል።
የቀረቡት ጉዳዮች ፦
~ የዐቃብያነ ህግ ደመዎዝና ጥቅማጥቅም ጉዳይ፣
~ በጸጥታ ችግር ምክንያት ከሥራ ቦታቸው ርቀው የነበሩና አሁን ላይ ለመመለስ ጥያቄ ያቀረቡ ዐቃብያነ ሕግ ጉዳይን፣
~ በደረጃ እድገት ያለፉ ዐቃብያነ ህግን ሹመት፣
~ በራስ ፍላጎት ከዐቃቤ ህግነት ሙያ የለቀቀ እና ለመመለስ የቀረበ ጥያቄ፣
~ በዲሲፕሊን ምክንያት ከስራ የተሰናበቱ ዐቃብያነ ህግ ጉዳይ፣ ናቸው።
በመሆኑም የጉባዔው አባላት፦
~ የዐቃብያነ ህግ ደመዎዝና ጥቅማጥቅምን ጉዳይ አስመልክቶ በየደረጃው የሚገኙ ዐቃብያነ ሕግ ሃገራዊ የደመወዝ ጭማሪን በተመለከተ ፍትህ ቢሮ የጀመረውን የማስፈፀም ሂደት እንዲቀጥልና በአጭር ጊዜ በታሰበው ልክ ምላሽ እንዲያገኝ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
~ በጸጥታ ችግር ምክንያት ከሥራ ቦታቸው ርቀው የነበሩና አሁን ላይ ለመመለስ ጥያቄ ያቀረቡ ዐቃብያነ ሕግ ጉዳይ በጥንቃቄ መርምሮ በቀጣይ የውሳኔ ሐሳብ እንዲቀርብ ፤
~ በደረጃ እድገት ያለፉ ዐቃብያነ ህግን ሹመት በተመለከተ ለዞን 17 እና ለክልል 4 በደረጃ እድገት ያለፉ እና የሥነ_ምግባር ችግር የሌለባቸው ዐቃብያነ ህግን ከሐምሌ 01/2018 ዓ/ም ጀምሮ ሹመት እንዲሰጣቸው፤
~ በራስ ፍላጎት ከዐቃቤ ህግነት ሙያ የለቀቀ እና ለመመለስ የቀረበ ጥያቄን ጉዳይ፣
~ በዐቃቤ ህግነት እና በዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊነት ለበርካታ አመታት ያገለገሉ እና በፈቃዳቸው ለቀው የነበሩ ወደ ተቋሙ ተመልሸ በሙያየ እንድሰራ ሲሉ በማመልከቻ የጠየቁ ከሐምሌ 01/2018 ዓ/ም ጀምሮ ተመልሰው በዞን ዐቃቤ ህግነት ተመድበው እንዲሰሩ፤
የሚል ውሳኔወችን ወስነዋል።
~ ሌላው የጉባዔ አባላት የአሰራር ና የዲሲፕሊን ግድፈት ፈጽመዋል በተባሉ ዐቃብያነ ህግ ላይ ጉዳዩን በስፋትና በጥልቀት በመወያየት የተለያዩ ውሳኔዎችን ወስነዋል።


